ከባቢሎን ጀርባ
ደማቅ ህብረ ቀለም የተስፋ ጽንሰቱ
ሞት ለሰው ተፈጥሮ ተስፋ ሞት ለሞቱ
ባቢሎን አካል ገዝቶ ከብዶብን ዳገቱ
መቃብር ላይጠግብ ሰው ሞትን ላይፈራ
ባቢሎን ሰው ሆኖ ሞት በሰው ሊዘራ
አለም ስትደነፋ ዘቦቿን ደምራ
የጭካኔን ሮሮ ስትዶልት ፎክራ
ያ የክፋት ጥጓን ባምላክ ላይ ስትሰራ
ቤልሆር ባንገቷ ላይ በማነቆ ይዟት
ባቢሎን በህይወቱ ላትጠፋ ተነቅሷት
ምንም ላትጠቅመው በጀርባው ታቅፏት
ፍቅር ላያሸንፍ ባቢሎን ሊረታ በከንቱ ሀሳብ ሙግት
ገምድረ ገጽ ጠፍቶ ይሰባበርና በእሳት ሰንሰለት ቤልሆር ይቀጣና
ተስፋ ያደረግናት ደማቅ ህብረ ቀለም ትውረድልን እና በፍጹም ትህትና
ከባቢሎን ፊት ላይ ወርደን ስንመለስ ወደ አፍሪካ ምድር እባክህ ውሰደን
እኛም እንድንመጣ ቤልሆርን ረግጠን ግንቡን አፈራርሰው ሲቃ የበዛበትን
ኖህን ያስደሰተው ያ ህብረ ቀለሙን አጉልተህ አሳየኝ ልለየው መንገዱን
ቀንበሩን ስበረው የክፋት መንገዱን ቤልሆር እንዳይገዛኝ
የኢትዮጵያ አምላክ የአፍሪካን ምድር ግፍ ክፉን አታሳየኝ
ከባቢሎን ጀርባ ቅደምልኝ እና በፍቅር አኑረኝ
Comments